የሀገር ውስጥ ዜና

ማዕድን ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው ሕዳር ወር በሚዘጋጀው ዓለም ዓቀፍ የማዕድን ኤክስፖ ላይ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

By Shambel Mihret

October 03, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጪው ሕዳር ወር ላይ በሚዘጋጀው ዓለም ዓቀፍ የማዕድን ኤክስፖ ላይ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በጋራ ለመሥራት ተስማምተናል ሲሉ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ በማህበራ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ የማዕድን ዘርፍ የብዙዎችን ትብብር ይጠይቃል ብለዋል፡፡

በተለይም እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ያሉ ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ለማዕድን ዘርፍ እድገት ዋና ባለድርሻ ናቸውም ነው ያሉት።

በዛሬው እለትም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ዋቄ እንዲሁም ከአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ጋር በማዕድን ዘርፍ ከአየር መንገዱ ጋር በትብብር በምንሰራቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተነጋግረናል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በመጪው ሕዳር ወር ላይ በሚዘጋጀው ዓለም ዓቀፍ የማዕድን ኤክስፖ̎ ላይ በጋራ ለመሥራት ተስማምተናል ሲሉ ገልጸዋል።