Fana: At a Speed of Life!

የሸለብታ የጤና በረከቶች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ10 ደቂቃ እስከ 30 ደቂቃ የሸለብታ ጊዜ መውሰድ ከድካም ስሜት እንዲወጡ እና የማስታወስ ችሎታ እንዲዳብር እንደሚረዳ የጤና ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

ሸለብታ ሰውነትን ዘና የማድረግ፣ ድካምን የመቀነስ ፣ንቁ እንዲሆኑ የማድረግ፣ መጥፎ ስሜትን የመቀየር፣ የፈጠራ ችሎታን የማዳበር ፣አዕምሮ በስራ እንዳይወጠር የማድረግ፣ ጤናማ እንዲሆኑ የማድረግ ፣በሽታን የመከላከል አቅምን የመጨመር፣ ጭንቀት እና ፍርሃትን የመቀነስ ፣ የማስታወስ ብቃታን የማሻሻል እና ሌሎች መሰል የጤና በረከቶች አሉት፡፡

አጭር የሸለብታ ጊዜ ስናሳልፍ ንቁ እና ጤናማ ሰው ሆነን የዕለት ከዕለት ስራችን በቅልጥፍና እንድናከናውን ከማድረጉም በላይ የሸለብታ ጊዜ ከማሳለፋችን በፊት ስላከናዎናቸው ÷ ትምህርት፣ ክህሎት፣ እውቀት እና ሌሎችንም ድርጊቶች በቀላሉ ለማስታወስ ይረዳል፡፡

መጥፎ ቀን እያሳለፍን ከሆነ ሸለብታ፥ ስሜትን ወደ ጥሩ መንፈስ የመቀየር ሀይል እንዳለው የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

ከ10 እስከ 30 ደቂቃ ባለው አጭር ጊዜ የሸለብታ ጊዜ ማሳለፍ በቂ ሲሆን የሸለብታ ጊዜው ከዚህ መርዘምም ሆነ ማጠሩ የሚገኘውን የጤና በረከት ይቀንሰዋል ነው የሚሉት የጤና ባለሙያዎች፡፡

ሸለብታ ከአነቃቂ መጠጦች (ካፌን) ከሚገኘው መነቃቃት የተሻለ የመነቃቃት ሀይል እንዳለው እና የማስታወስ ችሎታችንም እንደሚያዳብር ጥናቶችን ዋቢ ያደረገው የሄልዝ ላይን መረጃ ያመላክታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.