የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ታገሰ ጫፎና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዚዳንት ለስራ ጉብኝት አርባምንጭ ከተማ ገቡ

By Feven Bishaw

October 03, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ – ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሰለሞን አረዳ ለስራ ጉብኝት አርባምንጭ ከተማ ገብተዋል፡፡

አመራሮቹ አርባምንጭ ከተማ ሲገቡ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሥራ ኃላፊዎች እና የጋሞ ዞን ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል ።

እንግዶቹ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ስልጠና ላይ ይገኛሉ፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አርባምንጭ ማዕከል ይጎበኛሉ እንዲሁም የማዕከሉ የቁልፍ ርክክብ ያካሂዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከጋሞ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!