Fana: At a Speed of Life!

55 የአፍሪካ ሀገራት የሚሳተፉበት አህጉራዊ ኩነት በአዲስ አበባ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “አፍሪካ ለአፍሪካውያን” የተሰኘ 55 የአፍሪካ ሀገራት የሚሳተፉበት አህጉራዊ ኩነት በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡

አህጉራዊ ኩነቱን ለማካሄድ የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና አቢሲኒያ ቢዝነስ ኔትወርክ በጋራ በመሆን ዝግጅታቸውን እንዳጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

ኩነቱ ከጥቅምት 11 እስከ 13 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የሚካሄድ መሆኑን ከቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ባህሎቻቸውን እና አህጉራዊ እሴቶቻቸውን የሚያስዋውቁበት የአውደ ርዕይ መርሐ ግብር፣ የአውቶ እና የፋሽን ትዕይንት፣ የኪነ ጥበብ አውደ ርዕይ፣ የዳንስ እና የሙዚቃ ድግስ ያቀርባሉ ነው የተባለው።

በመላው አፍሪካ በሚገኙ ማህበረሰቦች ውስጥ ያሉትን የቢዝነስ፣ የቱሪዝም፣ የባህል፣ የኪነ ጥበብ፣ የኢንቨስትመንት፣ የንግድ እድሎችንና በዘርፉ ያለውን አቅም ለማስተዋወቅ የተመጠነ ዓመታዊ ዝግጅት እንደሆነም ተገልጿል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.