Fana: At a Speed of Life!

ኢጋድ በቀጠናው ሰላም እና ደህንነትን ለማረጋገጥ ለሚያደርገው ጥረት አባል ሀገራቱ ያላቸውን ድጋፍ ሊያጠናክሩ ይገባል – አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 23 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) አባል ሀገራት ድርጅቱ በቀጠናው ሰላም እና ደህንነትን ለማረጋገጥ ለሚያደርገው ጥረት ያላቸውን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቀረቡ፡፡

40ኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት አምባሳደሮች ኮሚቴ ስብሰባ በጅቡቲ ተካሂዷል፡፡

በስብሰባው የተገኙት አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ በወቅታዊ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በማብራሪያቸውም ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላም እና ደህንነትን እንዲሻሻል እንዲሁም የአካባቢው ሀገራት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንዲከበር ለማድረግ ላለው ጥረት የምታበረክተውን ሚና አጠናክራ እንደምትቀጥል አንስተዋል፡፡

የኢጋድ አባላ ሀገራትም ድርጅቱ ለቀጠናው ሰላም እና ደህንነት መረጋገጥ ለሚያደርገው ጥረት ያላቸውን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ነው ጥሪ ያቀረቡት፡፡

ከዚህ ባለፈም አባል ሀገራቱ በአካባቢው የሚያጋጥሙ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ችግሮችን በትብብር ለማለፍ የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

ኢጋድ በቀጣይ በአካባቢው ሰላም እና ደህንነት መረጋገጥ፣ በኢኮኖሚያዊ ትብብር፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባውም ጠቁመዋል፡፡

የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በበኩላቸው፥ አባል ሀገራቱ ለድርጅቱ ለሚያደርጉት ድጋፍ እና ትብብር አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

በቀጣይ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመቋቋምም አባል ሀገራቱ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.