Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እና የህንድ ስትራቴጂካዊ አጋርነት በትብብር መስኮች እንደሚጠናከር ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 23 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምሥራቅ ፣ኤስያ እና ፓስፊክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል አምባሳደር ገበየሁ ጋንጋ ከህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል አምባሳደር ቡኒት ኩንዳል ጋር ተወያይተዋል።
 
አምባሳደር ገበየሁ ጋንጋ÷ የህንድ እና የኢትዮጵያ ታሪካዊ ዘመናትን ያስቆጠረው ግንኙነት በኢኮኖሚና በባህላዊ መስኮች የቆየ ወዳጅነት እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
 
ይህ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዛሬ ላይ ዘርፈ ብዙ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተጠናክሮ መቀጠሉን ነው የገለጹት።
 
በቅርቡ የኢትዮጵያ እና የህንድ የምክክር ፎረም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ጠቁመው÷በህዝብ ለህዝብ ግንኘነት፣በባለብዙ ወገን ግንኘነት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይም በትብብር እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
 
አምባሳደር ቡኒት ኩንዳል በበኩላቸው÷ የሁለትዮሽ ግንኘነቱን ይበልጥ ለማሳደግ በኢንቨስትመንት፣ በንግድ በቴክኖሎጂ እንዲሁም በትምህርት ዘርፎች ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
 
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እንደመሆኗ እና በምስራቅ አፍሪካ ያላትን ተፅዕኖ ፈጣሪነት በመጠቀም በእድገት እና በልማት የትብብር ዘርፎች በጋራ እንሰራለን ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.