Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከከኮስ ሥራ አስፈጻሚ አባላት ጋር ተወያዩ

 

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 23 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራጭ ሴቶች (ኮከስ) ሥራ አስፈጻሚ አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡

 

በውይይታቸውም የሴቶችን ተጠቃሚነት እና ተሳታፊነት ከማረጋገጥ አኳያ ስለተከናወኑ የህግ ማውጣት፣ ክትትልና ቁጥጥር ስራዎች ላይ መክረዋል፡፡

 

ከዚህ ባለፈም በህዝብ ውክልና እና በፓርለማ ዲፕሎማሲ ዘርፍ እንዲሁም በሴት ተመራጮች ሚና ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.