Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሳይንስ ሙዚየምን መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሳይንስ ሙዚየምን መርቀው ከፈቱ።

ሙዚየሙ ሁለት ግዙፍ ህንጻዎች ሲኖሩት በሰባት ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ነው።

በሙዚየሙ ውስጥ ቋሚ እና ጊዜያዊ አውደ ርዕይ ማሳያዎች አሉት።

ሙዚየሙ ሳይንስ ጥበባዊ በሆነ መንገድ የሚገለጽበት ጥበብም ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚታይበት ነው ተብሏል።

ከተፈጥሮ ስርዓት ጋር ተስማሚ ሆኖ የተገነባው ሙዚየሙ ከጸሐይ ብርሀን የኤኤሌክትሪክ ሀይል ያገኛል።

የሙዚየሙ ውጫዊ ክፍል የቀለበት እና የጉልላት ቅርጽ እንዲኖረው ተደርጎ ነው የተገነባው፡፡

በዓላዛር ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.