Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ በጃፓን የዓየር ክልል የባላስቲክ ሚሳኤል አስወነጨፈች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ በጃፓን የዓየር ክልል የባላስቲክ ሚሳኤል ማስወንጨፏ ተገለጸ፡፡

የባሊስቲክ ሚሳኤሉ በፓሲፊክ ውቅያኖስ መውደቁ የተጠቀሰ ሲሆን ፥ ከመውደቁ በፊት 4 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር መጓዙ ተነስቷል፡፡

የተወነጨፈው መካከለኛ ርቀት ያለው ሚሳኤል ምንም ዓይነት ጉዳት አለማድረሱም ነው የተገለጸው።

ሰሜን ኮሪያ የቶኪዮ እና የዋሺንግተንን ትኩረት ለመሳብ ሆን ብላ ሚሳኤል አስወንጭፋለችም ነው የተባለው።

ከፈረንጆቹ 2017 በኋላም ሰሜን ኮሪያ በጃፓን የዓየር ክልል ስታስወንጨፍ የመጀመሪያው መሆኑም ነው የተገለጸው።

ይህን ተከትሎ ጃፓን ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ ያለቻቸውን ዜጎቿን እንዲጠነቀቁ ማሳሰቢያ ሰጥታለች፡፡

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ድርጊቱን “ጠብ አጫሪ” ሲሉ ኮንነውታል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰሜን ኮሪያ የባለስቲክ እና የኒውክሌር ጦር መሳሪያን እንዳትሞክር የከለከለ ሲሆን ፥ ያለ ምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ ወይም ምክክር ወደ ሌላ ሀገር ሚሳኤል መተኮስ ዓለም አቀፍ ህጎችን እንደሚቃረን ይታወቃል፡፡

የባለስቲክ ሚሳኤል ማስወንጨፍ የኒውክሌር ሙከራን ያህል ባይሆንም አስጊነቱ ላይ ግን አብዛኛው የዓለም ሀገራት የሚስማሙበት ነው፡፡

ጃፓን፣ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ባህር ሃይላቸውን ጨምሮ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ እያደረጉ ሲሆን፥ የአሁኑ የሰሜን ኮሪያ ሚሳዔል ሙከራም ለዚህ ምላሽ ሊሆን እንደሚችል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.