Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ ፓርላማ የቀድሞዎችን የዩክሬን አራት ግዛቶች የሩሲያ አካል አድርጎ ተቀበለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ፓርላማ የቀድሞዎችን የዩክሬን አራት ግዛቶች የሩሲያ ፌዴሬሽን አካል አድርጎ ተቀብሏል።

ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዶኔስክ፣ ሉሃንስ፣ ኬርሰን እና ዛፖሮዢየ የሩሲያ አካል እንዲሆኑ የሚያስችለውን ስምምነት ከየግዛቶቹ አስተዳዳሪዎች ጋር ከተፈራረሙ በኋላ በጉዳዩ ላይ ለመወሰን ተሰይሞ ነበር።

ይህን ተከትሎም የፓርላማው (ዱማ) አባላት ግዛቶቹ የሩሲያ ፌዴሬሽን አካል እንዲሆኑ በውሳኔያቸው አፅድቀዋል።

በፑቲን የተፈረመውን ስምምነት ህገ መንግስታዊው ፍርድ ቤትም አጽድቆታል።

ስምምነቱ ለመጨረሻ ዕይታ ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት እንደሚቀርብም አር ቲ በዘገባው አስታውሷል።

ግዛቶቹ ከፈረንጆቹ መስከረም 23 እስከ 27 ባካሄዱት ህዝበ ውሳኔ ሩሲያን ለመቀላቀል መወሰናቸው ይታወሳል።

ዩክሬን ህዝበ ውሳኔውን ሕገ-ወጥ ነው በሚል ለሂደቱ እውቅና እንደማትሰጥ መግለጻ የሚታወስ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.