በሰሜን ሸዋ ዞን አራት ወረዳዎች የማሽላ ጢንዚዛ ተከሰተ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አራት ወረዳዎች የማሽላ ጢንዚዛ መከሰቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።
እስካሁን 1 ሺህ 21 ሔክታር የማሽላ ሰብል ላይ ጢንዝዛ የተከሰተ ሲሆን÷ 966 ሔክታሩን በባህላዊ መንገድ ቀሪውን 55 ሔክታር ደግሞ በኬሚካል የመከላከል ሥራ መሠራቱ ተገልጿል፡፡
በመምሪያው የሰብል ልማት ቡድን መሪ አበበ ጌታቸው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በአንኮበር፣ ጣርማበር፣ ቀወት እና በረኸት ወረዳዎች የማሽላ ጢንዚዛ ተከስቷል፡፡
የቀበሌና የወረዳ ባለሙያዎች ጢንዚዛው በሰብሉ ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ÷ በባህላዊ ዘዴ በመልቀም፣ ማሽላውን በማወዛወዝና ጭስ በማጨስ እንዲሁም በኬሚካል የመከላከል ሥራ እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ጢንዚዛው ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሊስፋፋ እንደሚችል ትንበያ መኖሩን ጠቁመው÷ ወደ አጎራባች ወረዳዎች እንዳይዛመት ሁሉም አርሶአደርና ድጋፍ ሰጪ ባለሙያ የመከላከል ሥራው ላይ እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በሳምራዊት የስጋት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!