የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ክልል ለሃገር መከላከያ ሰራዊት ከ70 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ 

By Mikias Ayele

October 04, 2022

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ለሃገር መከላከያ ሰራዊት ከ70 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነትና የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን የደቡብ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎ ለመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሊዊጂ አስረክበዋል፡፡

በዚህ ወቅት አፈጉባኤዋ እንደተናገሩት ድጋፉ ከገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ የሰንጋ እና የተለያዩ ደረቅ ምግቦች ያካተተ ነው።

ድጋፉ ክህብረተሰቡ የተሰባሰበ ሲሆን የህወሓት ቡድን ለሶስተኛ ጊዜ የከፈተውን ጦርነት ለመመከት በግንባር እየተፋለመ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ደጀንነትን ለማሳየት የተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ማርታ ሊዊጂ በበኩላቸው ድጋፍ ላደረገው የክልሉ ህዝብ ምስጋናቸውን አቅርበው ህብረተሰቡ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ  ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡