Fana: At a Speed of Life!

የሳይንስ ሙዚየሙ ከተማችንን በቴክኖሎጂ የበለፀገች ከተማ በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው – ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ የተመረቀው የሳይንስ ሙዚየም ከተማችንን በሳይንስና በቴክኖሎጂ የበለፀገች ከተማ (ስማርት ሲቲ) በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡

ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመዲናዋ የተገነባውን የሳይንስ ሙዚየምን መርቀው መክፈታቸው ይታወቃል፡፡

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ ዛሬ የተመረቀው የሳይንስ ሙዚየም ከተማችንን ስማርት ሲቲ በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ፤ ይህም በቴክኖሎጂና በሳይንስ የልህቀት ማዕከል ሆኖ ሊያገለግል የሚችል ነው ብለዋል ።

የከተማዋ ነዋሪዎችም በተለይም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዝንባሌ ያላቸው መጥተው እንዲጎበኙም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

“ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ይህን መሰለ የከተማችንን ገጽታ ከፍ የሚያደርግ የልህቀት ማዕከል ፕሮጀክት በመስራት ትውልዱ በሳይንስና ቴክኖሎጂ መርምር እንዲጎለብት ስላበረከቱልን በእጅጉ እናመሰግናለን” ሲሉም በፅሁፋቸው አስፍረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.