የሀገር ውስጥ ዜና

የሳይንስ ሙዚየሙ ከተማችንን በቴክኖሎጂ የበለፀገች ከተማ በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው – ከንቲባ አዳነች

By Meseret Awoke

October 04, 2022

ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመዲናዋ የተገነባውን የሳይንስ ሙዚየምን መርቀው መክፈታቸው ይታወቃል፡፡

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ ዛሬ የተመረቀው የሳይንስ ሙዚየም ከተማችንን ስማርት ሲቲ በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ፤ ይህም በቴክኖሎጂና በሳይንስ የልህቀት ማዕከል ሆኖ ሊያገለግል የሚችል ነው ብለዋል ።

የከተማዋ ነዋሪዎችም በተለይም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዝንባሌ ያላቸው መጥተው እንዲጎበኙም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

“ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ይህን መሰለ የከተማችንን ገጽታ ከፍ የሚያደርግ የልህቀት ማዕከል ፕሮጀክት በመስራት ትውልዱ በሳይንስና ቴክኖሎጂ መርምር እንዲጎለብት ስላበረከቱልን በእጅጉ እናመሰግናለን” ሲሉም በፅሁፋቸው አስፍረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!