Fana: At a Speed of Life!

የመስህብ ስፍራዎችን ለማልማት የግሉ ዘርፍ እንዲሳተፍ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስህብ ስፍራዎችን ለማልማት የግሉ ዘርፍ እንዲሳተፍ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ጣሂር መሀመድ ጥሪ አቀረቡ፡፡

በአማራ ክልል ያሉ የመስህብ ስፍራዎች በርካታ በመሆናቸው መንግስት ብቻውን ማልማት አይችልም ያሉት ኃላፊው ፥ የግሉም ዘርፍ በስፋት ሊሳተፍ ይገባል ብለዋል፡፡

በተለይም እንደ ግሸን ደብረ ከርቤ ያሉ ታሪካዊ፣ ሃይማኖታዊ እና መልከአ ምድራዊ ሀብቶች በመንግስት ብቻ ሳይሆን የሲቪክ ማህበራት፣ የግል ባለሀብቶችና የሃይማኖት ተቋማትን ትብብር ይጠይቃሉም ነው ያሉት፡፡

የግሸን ደብረ ከርቤን መንገድ ለማሠራት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እያደረግን ነው ያሉት አቶ ጣሂር ፥ ገዳሟንና በገዳሟ ስር ያሉ ቅርሶችን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፥ ባህልና ሳይንስ ተቋም ለማስመዝገብ የሃይማኖት መሪዎች ተነሳሽነትና የአካባቢው ማህበረሰብ ይሁንታ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በክልሉ ተጀምሮ የነበረውን ‘መሥቀልን በመስቀለኛ ቦታ’ መርሐ ግብርን በማስታወቂያና ፕሮሞሽን ሙያ የተሠማሩ፥ በገዳማት ጉዞና ጉብኝት የሚሳተፉ አካላት ቢጠናከሩ ክልሉ ድጋፍ እንደሚያደርግም ነው የገለጹት፡፡

በአለባቸው አባተ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.