የሀገር ውስጥ ዜና

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከድሬዳዋ ከተማ ካቢኔ ጋር መከሩ

By Mikias Ayele

October 04, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይታቸውን አስመልክተወ ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሉት ፥ ከሥራ ዕድል ፈጠራ እና ከኢንዱስትሪ ሰላም አኳያ ያሉ አዲስ እሳቤዎችን በተመለከተ ምክክር አድርገናል፡፡

የ2015 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫዎች በተመለከተ እንዲሁም አስተዳደሩ ከዘርፉ አንፃር እያከናወነ ያለውን ስራ በተመለከተ ውይይት መደረጉንም ነው የገለጹት፡፡

በቆይታቸውም በኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ክህሎት ለትራንስፎርሜሽንና ቀጠናዊ ትሥሥር ኘሮጀክት እየተገነቡ ከሚገኙ ሰባት የልህቀት ማዕከላት አንዱ የሆነው የድሬደዋ ልህቀት ማዕከልም በጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝ ተረድተናል ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!