Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ በጎርፍ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ከተማ በጎርፍ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የተለያየ ምግብ ነክ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

የባሮ፣ ጀጀቤእና ሌሎች መጋቢ ወንዞች በዘንድሮው የክረምት ወራት በከፍተኛ ሁኔታ መሙላታቸውን ተከትሎ በርካቶች መፈናቀላቸው ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም ለተፈናቀሉ ወገኖች ባለሃብቶችን ጨምሮ የተለያዩ ድርጅቶች ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ተናግረዋል፡፡

የክልሉ መንግሥትም በጎርፍ የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ 10 ሚሊየን ብር ለግሷል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

በክልሉ መንግሥት የሚደረጉ ድጋፎች በቂ ባለመሆናቸው ሌሎች አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የክልሉ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር አገልግሎት ሩዝና መሠል ምግብ ነክ ድጋችፎን ማድረጉም ተገልጿል፡፡

የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማሪያም እንደገለጹት፥ በጎርፍ አደጋው ለተጎዱ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና የአጭርና የረጅም ጊዜ መፍትሔ ለመስጠት ይሠራል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.