በሐረሪ ክልል ለሥራ ፈጣሪዎች ሥልጠና መስጠት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደረገ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራ እና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በሐረሪ ክልል ለሥራ ፈጣሪዎች የተለያዩ ሥልጠናዎችን መስጠት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከክልሉ የካቢኔ አባላት ጋር ተወያዩ፡፡
ሚኒስትሯ በውይይታቸው፥ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ፣ በቱሪዝም ፣ በባሕላዊ አልባሳት እና ሥራ ፈጣሪዎች በፈጠሩት ሥራ ውጤታማ መሆን በሚቻልበት አግባብ እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል ።
ሙያዊ ክኅሎት ለማደበር ስለሚሰጡ ሥልጠናዎችም ከተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ጋር መምከራቸውን እና ስምምነት ላይ መደረሱን ወይዘሮ ሙፈሪሃት ጠቁመዋል፡፡
የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፥ አምራች የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል እየተሠሩ ያሉት ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ተናግረዋል።
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለሚሰራቸው ሥራዎች በሙሉ ክልሉ አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብርን እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል፡፡
በነስሪ ዩሱፍ