የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ምክር ቤት አባል ሆና ተመረጠች

By Mekoya Hailemariam

October 05, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ምክር ቤት አባል ሆና ተመረጠች።

193 ሀገራትን በአባልነት የያዘው የዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት በካናዳ ሞንትሪያል ጉባኤውን አካሂዷል።

ኢትዮጵያን በመወከልም የኢፌዴሪ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ ተሳትፈዋል።

በዚህ ጉባኤም ኢትዮጵያ የድርጅቱ ምክር ቤት አባል ሆና መመረጧን ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊ ገልፀዋል።