Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ወሎ ዞን ለመከላከያ ሰራዊት ከ41 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ወሎ ዞን ለመከላከያ ሰራዊት ከ41 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉ በደቡብ ወሎ ዞን ከሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተሰበሰበ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር የተሰበሰበውን የአይነት ድጋፍ ግንባር ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት በቆቦ ከተማ ተገኝቶ አስረክቧል፡፡

ድጋፉም÷ የእርድ እንስሳትና ደረቅ ሎጂስቲክ ሲሆን ከ2 ሺህ 100 በላይ በግና ፍየል እንዲሁም 183 የእርድ ሰንጋን ጨምሮ ምግብ ነክ ቁሳቁስ ያካተተ ነው፡፡

በከድር መሀመድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.