Fana: At a Speed of Life!

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የመንገድ ድጋፍ ግንብ ተደርምሶ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ወንጌላዊት አካባቢ በደረሰ የመንገድ ድጋፍ ግንብ መደርመስ አደጋ በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ።
የመንገድ ድጋፍ ግንብ በመኖሪያ ቤት ላይ ሲደረመስ በቤታቸዉ ተኝተዉ የነበሩ እድሜያቸዉ 35 እና የ7 ዓመት እናትና ልጅ ወዲያዉ ህይወታቸዉ ማለፉ ነው የተገለጸው።
ከእሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ባገኘነው መረጃ፥ የድጋፍ ግንቡ መፍረሱን ተከትሎ የኮብልስቶን መንገዱም መሰረቱ ጭምር ተደርምሶ በቤቱ ላይ አርፎ አደጋዉን አባብሶታል።
የመኖሪያ ቤቱ ከድጋፍ ግንቡና ከመንገዱ አምስት ሜትር ገደማ ዝቅ ብሎ የሚገኝ እንደሆነም ነው የተጠቆመው።
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችም የአካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም የጸጥታ አባላት የሟቾችን አስከሬን ከፍርስራሽ ውስጥ አውጥተዋልም ተብሏል፡፡

 

በአደጋው በቤቶች ውስጥ የነበሩ አራት ሰዎች ከአደጋዉ አምልጠዉ እራሳቸውን ማትረፍ ሲችሉ ፥ በአደጋዉ ሦስት መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋልም ነው የተባለው።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.