Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ከጋቪ ክትባት ህብረት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ2020 ጀምሮ የጋቪ ሻምፒዮን ሆነው የቆዩት ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የጋቪ ክትባት ህብረት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ሴት በርክሌይን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

ውይይቱ በኢትዮጵያና በጋቪ መካከል ስላለው አጋርነትና ምንም ክትባት ወስደው የማያውቁ “ዜሮ ዶዝ” ህፃናትን ለመድረስ ጋቪ ከ2021-2025 የያዘውን ስትራቴጂያዊ ራዕይ በተመለከተ ኢትዮጵያ በምታደርገው ድጋፍ ላይ ያተኮረ እንደሆነም ነው የተገለጸው።

ጋቪ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ 2ኛ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ የምታገኝ ሀገር መሆኗን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ለሚያደርገው ድጋፍ አመስግነው ፥ ኢትዮጵያ የክትባት ሽፋንን ለመጨመር ያላትን ቁርጠኝነት ማረጋገጣቸውም ነው የተገለጸው።

በውይይቱ ወቅት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ተገኝተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.