Fana: At a Speed of Life!

የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር እና ኢንኮሞኮ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በቢዝነስ ስልጠናዎችና የማማከር አገልግሎት በመስጠት ከሚታወቀው ኢንኮሞኮ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማምቷል፡፡

የቢዝነስ አማካሪና የኢንቨስትመንት ተቋም የሆነው ኢንኮሞኮ ስደተኞች ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ነው ።

ተቋሙ በአዲሱ ስትራቴጂው ጥቃቅንና ማይክሮ ኢንተርፕራይዞችን ለማገዝ 21 ቢሊየን ብር ኢንቨስት እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡

መርሐ ግብሩ እስከ ፈረንጆቹ 2030 የሚቆይ ሲሆን ÷ በስምንት ሀገራት ተግባራዊ እንደሚደረግም ተጠቁሟል፤፡

ኢንኮሞኮ ባለፋት 10 ዓመታት በኢትዮጵያና ሩዋንዳ ለ41 ሺህ በላይ ስራ ፈጣሪዎችን እገዛ ማድረጉ ነው የተመላከተው፡፡

በኢትዮጵያ ጅግጅጋ፣ አዲስ አበባና አሶሳ ከተሞች ላይ እየሰራ የሚገኘው ኢንኮሞኮ÷ ካለፈው ሚያዚያ ወር ጀምሮ ኢንተርፕራይዞች ብድር በሚያገኙበት መንገድ ዙሪያ ከዳሽን ባንክ ጋር እየሰራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

ኢንኮሞኮ በኢትዮጵያ 150 ሺህ ጥቃቅንና ማይክሮ ኢንተርፕራይዞችን ሊያግዝ የሚያስችል ስትራቴጂ ዙሪያ ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር ውይይት ማድረጉን የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ንጉሱ ጥላሁን ገልጸዋል።

በማህሌት ተ/ ብርሃን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.