Fana: At a Speed of Life!

ወደፊትለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ላይ አፋጣኝ ሥራ ሊሠራ እንደሚገባ አቶ አወል አርባ አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ላይ የተሻለ አፋጣኝ የመከላከል ሥራ ሊሠራ እንደሚገባ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ አሳሰቡ፡፡

በአፋር ክልል በጎርፍ የሚከሰቱ ጉዳቶችን ለመቆጣጠር እየተሠሩ በሚገኙ ሥራዎች ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተወያይተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት÷ በጎርፍ ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎችና ወደፊት ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ላይ የተሠሩ ሥራዎች አበረታች ናቸው፡፡

ከዚህ በተሻለ መልኩ አፋጣኝ ሥራዎች ሊሠሩ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ወደፊት ሊሠሩ የሚገቡ ሥራዎችን በተመለከተም አቅጣጫ መቀመጡን የርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በውይይቱ ላይ የክልሉ መስኖና ተፋሰስ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዋላእ ዊቲካ÷ በጎርፍ የደረሱ አደጋዎችን ለመመከት እየተሠሩ የሚገኙ ሥራዎችና የደረሱ ጉዳቶችን የተመለከተ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.