Fana: At a Speed of Life!

አራት የዩክሬን ግዛቶች ወደ ሩስያ በይፋ ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አራት የዩክሬን ግዛቶችን ወደ ሩሲያ ማዋሃድ የሚያስችለውን የመጨረሻ ስምምነት ፈርመዋል፡፡

ፑቲን ከዶኔስክ እና ሉሃንስክ ሕዝብ ሪፐብሊኮች እንዲሁም ከኬርሰን እና ዛፖሮዢዬ ክልሎች ጋር አራት የውህደት ስምምነቶችን ፈርመዋል።

20 በመቶ የዩክሬን ክፍል ይሸፍናሉ የሚባሉት አራቱ ግዛቶች÷ ባለፈው ሣምንት ከሩስያ ጋር ለመዋሃድ ሕዝበ ውሳኔ ማካሄዳቸው ይታወሳል።

የሕዝበ ውሳኔው ውጤት እንዳመላከተው፥ በአማካይ ከ94 በመቶ በላይ የየግዛቶቹ ነዋሪዎች ሩስያን ለመዋሃድ ወስነዋል፡፡

በዚህም ግዛቶቹ በይፋ የሩስያ አካል እንዲሆኑ የሕገ መንግሥታዊው ፍርድ ቤት እና የሩስያን ፓርላማ (ዱማ) አጽድቋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ስምምነቱ የሩስያን ሕግ የተከተለ ነው በሚል ከገመገመና ካጣራ በኋላ ለምክር ቤቱ መምራቱን ተከትሎ÷ ለፌደሬሽን ( ለላይኛው ምክር ቤት) ቀርቦ ይሁንታ በማግኘቱ ግዛቶቹ በይፋ የሩስያ አካል ሆነው ይቀጥላሉ መባሉን አርቲ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.