Fana: At a Speed of Life!

የፌዴሬሽን ም/ቤት ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም መደበኛ ጉባዔውን ያካሂዳል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ፌዴሬሽን ምክር ቤት ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም 6ኛ የፓርላማ ዘመን 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን እንደሚያካሂድ ተገለጸ፡፡

የምክር ቤቱ ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ተረፈ በዳዳ እንደገለጹት÷ ምክር ቤቱ በመደበኛ ጉባዔው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጋራ መክፈቻ ጉባዔያቸውን እንደሚያካሂዱ የፌደሬሽን ምክር ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን ከማካሄዱ አስቀድሞ÷ የምክር ቤቱ አራት ቋሚ ኮሚቴዎች ከጉባዔው አጀንዳዎች ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ አቶ ተረፈ ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.