የሀገር ውስጥ ዜና

ሚኒስቴሩ የ12ኛ ክፍል የእስልምና እምነት ተከታይ ተፈታኞች የመውሊድ በዓልን አክብረው መስከረም 29 ቀን መግባት እንደሚችሉ አስታወቀ

By Meseret Awoke

October 05, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል የእስልምና እምነት ተከታይ ተፈታኝ ተማሪዎች መስከረም 28 የመውሊድ በዓልን አክብረው መስከረም 29 ቀን 2015 ዓ.ም መግባት እንዲችሉ በልዩ ሁኔታ መፈቀዱን አስታውቋል፡፡

መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ለሚጀምረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች መስከረም 26 እስከ 28 ተጠቃለው በመግባት መስከረም 29 ቀን ስለፈተናውና ተያያዥ ጉዳዮች በየተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ገለጻ የሚደረግበት ዕለት መሆኑን መግለጹ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ የእስልምና እምነት ተከታዮች መስከረም 28 ቀን የመውሊድ በዓል አክብረዉ መስከረም 29 ቀን 2015 ዓ.ም እሁድ ጠዋት መግባት እንዲችሉ በልዩ ሁኔታ የተፈቀደላቸው መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡

በተጨማሪም የፈተና እና ተያያዥ ጉዳዮች ገለጻ ይህንን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እሁድ ከሰዓት በኋላ እንዲሰጥ መደረጉ ተገልጿል፡፡

የእምነቱ ተከታይ ተማሪዎችም ይህንን አውቀው በተጠቀሰው ሰዓት በመገኘት ገለጻ እንዲከታተሉም ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!