Fana: At a Speed of Life!

ከ200 በላይ የዚምባቡዌ መምህራን በሩዋንዳ ሥራ ሊጀምሩ ነው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በያዝነው የፈረንጆች ወር ከ200 በላይ የዚምባቡዌ መምህራን በሩዋንዳ በሚገኙ የትምህርት ተቋማት ሥራ እንደሚጀምሩ ተገለጸ፡፡

ይህም በሀገሪቷ ያለውን የመምህራን እጥረት ለመቅረፍ የሚደረገው ጥረት ከፊል ማሳያ መሆኑን ሲጂቲ ኤን ዘግቧል።

መምህራኑ÷ በምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ለመቀጠር በቅድመ ሁኔታ የሚወሰዱትን ፈተናዎች በተሳካ ሁኔታ ማለፋቸው ተገልጿል፡፡

በቆይታቸውም በመሰረታዊ ትምህርት፣ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ፣ በተግባረ ዕድ እና በጤና ዘርፎች ላይ ያላቸውን ዕውቀት ለተማሪዎቻቸው እንደሚያካፍሉ ተጠቁሟል፡፡

የሩዋንዳ ትምህርት ሚኒስቴር እንደገለጸው÷ መምህራኑ በመጀመሪያ የሦስት ዓመት የቅጥር ኮንትራት እንደሚፈጸምላቸውና በየዓመቱ አፈጻጸማቸው እየታየ የሚታደስ ይሆናል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.