Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ።

የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ሲገቡ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው “እንኳን ደህና መጡ” በማለት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ከአቀባበሉ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በሀገራቱ መካከል ያለው ግንኙነት በጋራ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ፣ በጠንካራ መሰረት ላይ የተገነባ እና በትብብር ላይ የተመሰረተ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ በሁለትዮሽና የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፕሬዚዳንቱ በቅርቡ በኬንያ በተደረገው ሀገራዊ ምርጫ ራይላ ኦዲንጋን በማሸነፍ ስልጣን መያዛቸው ይታወሳል።

በዓላዛር ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.