Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ ተጨማሪ ባላስቲክ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ ሁለት ተጨማሪ የአጭር ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን በዛሬው ዕለት አስወንጭፋለች፡፡

ፒዮንግያንግ ÷አሜሪካ ተዋጊ ወታደሮቿን እና የጦር ተሸካሚ መርከቧን በኮሪያ ልሳነ ምድር በድጋሚ ማሰማራቷን ተከትሎ ነው የአጭር ርቀት ባላስቲክ ሚሳኤሎችን ያስወነጨፈችው፡፡

ከዚህ ባለፈም አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ሰሞኑን ላደረጉት ወታደራዊ ልምምድ የተሰጠ አፀፋዊ ምላሽ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ይህም ሰሜን ኮሪያ በ12 ቀናት ውስጥ ያስወነጨፈቻቸውን ባላስቲክ ሚሳኤሎች ቁጥር ስድስት አድርሶታል ነው የተባለው፡፡

በመጀመሪያ የተወነጨፈው ሚሳኤል 350 ኪሎ ሜትር ወይም 217 ማይል የተምዘገዘገ ሲሆን÷ ሁለተኛው ደግሞ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት መወንጨፉ ተነግሯል፡፡

ሰሜን ኮሪያ በኮሪያ ልሳነ ምድር የሚካሄደው የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ለጦርነት የሚደረግ ዝግጅ ከመሆኑ ባሻገር በሉዓላዊነቷ የተደቀነ ስጋት መሆኑን በተደጋጋሚ ገልጻለች፡፡

ሰሞኑን አሜሪካ ፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ ያደረጓቸው ወታደራዊ ልምምዶችም ሰሜን ኮሪያን በእጅጉ እንዳስቆጣት ፕረስ ቲቪ በዘገባው አስታውሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.