Fana: At a Speed of Life!

ሳፋሪኮም የደንበኞች የኔትወርክ አገልግሎት በአዲስ አበባ በይፋ አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞች የኔትወርክ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ በይፋ አስጀምሯል፡፡

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ባካሄደው የደንበኞች የኔትወርክ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን ለማስጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡

በማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይም የተቋሙ የስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሳኡሳ፥ ኩባንያው ወደ ስራ እንዲገባ እገዛ ላደረጉ ለኢትዮጵያ መንግስት አካላት እና ለሌሎች ባለድረሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ የራሱን አስተዋጽኦ ለማበረከት እና ተደራሽነቱን ለማስፋት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ሳፋሪኮም ባለፉት ሳምንታት በድሬዳዋ፣ ባህርዳር፣ አወዳይ፣ ጎንደር ፣ሞጆ፣ ሐረር፣ አዳማ፣ ሀረር፣ ቢሾፍቱና ደብረ ብርሃን ከተሞች የኔትዎርክ ሙከራ አገልግሎቱን መጀመሩንም ከኩባንያው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.