Fana: At a Speed of Life!

የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን አቅም ማሳደግ ፍላጎትን የሚመጥን አቅርቦት እንዲኖር ያግዛል-ኢ/ር ታከለ ኡማ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዳዲስ ፋብሪካዎችን ከመገንባት በተጨማሪ ያሉንን የሲሚንቶ ፋብሪካዎች አቅም ማሳደግ ፍላጎትን የሚመጥን አቅርቦት እንዲኖር ያግዛል ሲሉ የማዕድን ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ ገለጹ፡፡

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በድሬደዋ ከተማ የሚገኘውን እና የጥገና ሥራው የተጠናቀቀውን ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካን ጎብኝተዋል፡፡

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የፋብሪካው እህት ኩባንያ የሆነው እና በግንባታ ላይ የሚገኘውን ለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሪፖርት ተመልክተናል ብለዋል፡፡

የናሽናል ሲሚንቶ ጥገና የፋብሪካውን የማምረት አቅም 30 በመቶ እንደሚያሳድገው ኢንጂነር ታከለ ገልጸዋል፡፡

አዳዲስ ፋብሪካዎችን ከመገንባት ባሻገር ያሉንን የሲሚንቶ ፋብሪካዎች አቅም ማሳደግ ፍላጎትን የሚመጥን አቅርቦት እንዲኖር ያግዛል ሲሉም ነው ያሉት፡፡

ከድሬዳዋ ከንቲባ ከድር ጁሀር ጋር በከተማዋ ስላለው የማዕድን ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ላይ መወያየታቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በከተማዋ ያለውን የማዕድን አቅም ለመጠቀምና ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ብረቶችን በከተማዋ ለሚገኙ የብረት ፋብሪካዎች ግብዓት እንዲቀርቡ መስማማታቸውንም አስታውቀዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.