ሚኒስቴሩ የመውሊድ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋራ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የመውሊድ በዓልን ምክንያት በማድረግ አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር አካሄዷል፡፡
የሚኒስቴሩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዲሳ ያደታ ደጋፊና ረዳት ለሌላቸው ነዋሪዎች የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም በእቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው÷ የዛሬው ለሁለተኛ ጊዜ እንደተደረገ አንስተዋል፡፡
ሚኒስቴሩ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ አቅም ለሌላቸው ነዋሪዎች የምግብ ዘይት፣ ዱቄት እና ስኳር ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰዋል፡፡
የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዋለለልኝ ቦጋለ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በቀጣይ በክፍለ ከተማው ያሉ መሰል ችግሮችን ለመፍታት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ መገለጹንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!