Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከ7 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሁለት ሜጋ ፕሮጀክቶችን ግንባታ ለማካሄድ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ7 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሁለት ሜጋ ፕሮጀክቶችን ግንባታ ለማካሄድ የፊርማ ስነስርዓት ተከናወነ፡፡
 
የመጀመሪያው ከ6 ነጥብ 1ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሁለት ፕሮጀክትና በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አንድ ፕሮጀክት የሚገነቡ የግብርና ምርቶች መሸጫ ማዕከላት ግንባታ ነው ተብሏል፡፡
 
ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በመዲናዋ አስተማማኝ የግብርና ምርት አቅርቦት እንዲኖር የሚያግዝና ገበያውን በማረጋጋት ለአምራቹ እና ለሸማቹ ተመጣጣኝ ምርቶች እንዲቀርቡ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
ሁለተኛው በ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በሆነ ወጪ የጤናውን ዘርፍ ለማሳደግ በተያዘው ቁርጠኝነት የሚገነባው የዘውዲቱ ሆስፒታል ማስፋፊያ የB+G+8 ፕሮጀክት ግንባታ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ግንባታው፥ 200 ህሙማንን የሚያስተናግዱ አልጋዎች፣ 27 የድንገተኛ ህክምና መስጫ ክፍሎች እንዲሁም የቀዶ ጥገናና የፊዚዮቴራፒ ህክምናዎችን ጨምሮ የስብሰባ አዳራሾችን ያካተተ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው በኩል አስታውቀዋል።

ፕሮጀክቶቹ ኦቪድ ግሩፕ እና በተስፋዬ ኃይሌ ኮንስትራክሽን ኩባንያዎች ይገነባሉም ተብሏል።

የፕሮጀክቶቹን ግንባታ በታቀደው ጊዜ ገደብ በፍጥነትና በጥራት በማጠናቀቅ ለሕዝብ ጥቅም እንዲውሉ ከንቲባ አዳነች አሳስበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.