የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ የኢትዮጵያ መንግስት ለሳፋሪኮም የሞባይል ገንዘብ ዝውውር እንዲያደርግ በመፍቀዱ የተሰማቸውን ደስታ ገለጹ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ የኢትዮጵያ መንግስት ለሳፋሪኮም የሞባይል ገንዘብ ዝውውር እንዲያደርግ በመፍቀዱ የተሰማቸውን ደስታ ገለጹ።
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢንተርኔት አገልግሎት ማስጀመሪያ መረሐ ግብር በወዳጅነት አደባባይ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ ላይ ለኩባንያው በሞባይል የገንዘብ ዝውውር እንዲያከናውን እንደተፈቀደ ይፋ ሆኗል።
ይህን ተከትሎም ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፥ “የኬንያ ህዝብ ወደ ኢትዮጵያ ስመጣ ይህን እንዳስፈጽም የቤት ስራ ሰጥቶኝ ነበር፤ የኢትዮጵያ መንግስት ይህን አገልግሎት በመፍቀዱ አመሰግናለሁ” ብለዋል።
ሳፋሪኮም በኬንያ በኤም ፔሳ የገንዘብ አገልግሎት ያገኘውን ስኬት በኢትዮጵያ ለመድገም እንደሚሰራም አስታውቋል።
ኢትዮ ቴሌኮም ከዚህ ቀደም የቴሌ ብር አገልግሎት በማስጀመር ሚሊዮኖችን ተጠቃሚ ማድረጉ ይታወሳል።
በብስራት መለሰ