Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሀመድ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ከሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በልማት፣  በስራ ስምሪትና የስራ ዕድል ፈጠራ ልማት ዙሪያ በጋራ ለመስራት መምከራቸውን  ወ/ሮ ሙፈሪሃት  በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በተጨማሪም በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በኢንዱስትሪ ግንኙነት የትብብር መስኮች በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ  ማስቀመጣቸውን ጠቁመዋል፡፡

የክልሉን መልካም የሰላም ግንባታ  እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም የክልሉ  ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ በትብብር  ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱንም  አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.