Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ የአርሶ አደሩን ጥያቄዎች ለመመለስ በትኩረት ይሰራል – ወ/ሮ ሚስራ አብደላ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል የአርሶ አደሩን ጥያቄዎች ለመመለስና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል ሲሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሚስራ አብደላ ተናገሩ፡፡

የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮው የ2014 የበጋ መስኖ ልማት እቅድ አፈጻጸምና የ2015 የበጀት አመት ዕቅድን ማስጀመሪያ በዛሬው ዕለት ገምግሟል፡፡

በግምገማውም የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሚስራ አብደላ እንደገለጹት ፥ በ2014 ባጀት ዓመት በበጋ መስኖ ልማት ዘርፉ ውጤታማ ተግባራት ተከናውኗል፡፡

ባለፈው የበጀት ዓመት በተከናወኑ ተግባራት የተገኙ መልካም አፈጻጸሞችን ለማስቀጠልና ክፍተቶችን ለመቅረፍ የክትትልና የድጋፍ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ነው ያሉት።

በተያዘው የ2015 የበጀት ዓመትም አርሶ አደሩ የሚያነሳቸውን የማዳበሪያ፣ የሃይል አቅርቦት፣ የምርጥ ዘር ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለመቅረፍና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በ2015 የበጀት ዓመት የበጋ መስኖ ልማት ከ2014 አፈጻጸም የተሻለ ለማድረግ በቅንጅት መንቀሳቀስ አስፈላጊ ነው ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.