Fana: At a Speed of Life!

የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በኢትዮጵያ የነበራቸውን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በኢትዮጵያ የነበራቸውን ይፋዊ የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ፕሬዚዳንቱ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አሸኛኘት አድርገውላቸዋል፡፡

በፕሬዚዳንቱ የተመራው ልዑካን በኢትዮጵያ በነበረው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርጓል።

በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት እና የድንበር አካባቢ ንግድን ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸው ተገልጿል፡፡

ከዚህ ባለፈም ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በመሆን በቅርቡ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነውን ሳይንስ ሙዚየምን ጎብኝተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.