Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ስንዴ እንድትልክ የሚያስችል ስምምነት ተደረሰ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ወደ ኬንያ የስንዴ ምርት እንድትልክ የሚያስችል ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መሪዎች መካከል ተደረሰ፡፡

ሰምምነቱ የተደረሰው የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በይፋዊ የስራ ጉብኝታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

የኬንያ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀው፥ የስንዴ አቅርቦት ስምምነቱ በኬንያ የተከሰተውን የምግብ ምርቶች የዋጋ ንረት ለማረጋጋት አስተዋፅኦ ይኖረዋል።

ከስንዴ አቅርቦት ስምምነቱ በተጨማሪ መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ አቅም ለመጠቀም በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ተገልጿል፡፡

በአጠቃላይ የሁለቱን የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እና የድንበር ተሻጋሪ ንግድን ለማሳደግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.