የሀገር ውስጥ ዜና

የመውሊድ በዓል የሚከበርበትን ስፍራ የማጽዳት ስራ ተካሄደ

By Feven Bishaw

October 07, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ከአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ጋር በመተባበር የመውሊድ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአንዋር መስጂድ የጽዳት መርሐ ግብር አካሂዷል፡፡

 

በመርሐ ግብሩ የከተማና የክፍለ ከተማ አመራሮችን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች፣ አርቲስቶች ፣ የጽዳት አምባሳደሮች ፣በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እና ሌሎች የመዲናዋ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

 

በሁሉም ክፍለ ከተሞችም በዓሉ የሚከበርበትን የመስጂድ ቦታ እና አካባቢውን የማፅዳት መርሐ ግብር መካሄዱን ከአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡