Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ የቤት ኪራይ መጨመርም ሆነ ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ውሳኔ ለ5 ወራት ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የቤት ኪራይ መጨመርም ሆነ ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ውሳኔ ለሚቀጥሉት አምስት ወራት ተራዘመ፡፡

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በሳምንታዊ ስብሰባው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

አስተዳደሩ ከሰኔ 2014ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ወራት የቤት ኪራይ መጨመርና ተከራይን ማስወጣት የሚከለክል ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡

ስለሆነም ወቅታዊ የሀገሪቱን ሁኔታ እና የኑሮ ውድነት ከግምት በማስገባት በተከራይ ላይ የኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ከቤት ማስወጣት የሚከለክለው ውሳኔ ለሚቀጥሉት አምስት ወራት ተፈጻሚ ሆኖ እንዲቀጥል ካቢኔው ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በተጨማሪም ካቢኔው በገበያ ትስስር ለኢንተርፕራይዞች ስለሚሰጥ የዋስትና ሽፋን መመሪያ እና የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ፍኖተ ካርታን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን የድሬዳዋ ከተማ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.