የሀገር ውስጥ ዜና

አምራች ተተኪዎችን ለማፍራት ለወጣቶች ጤና ትኩረት እንደሚሰጥ ተገለጸ

By ዮሐንስ ደርበው

October 07, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጤናማ እና አምራች ተተኪዎችን ለማፍራት ለአፍላ ወጣቶች እና ወጣቶች ጤና በትኩረት እንደሚሠራ ተገለጸ፡፡

በጤናው ዘርፍ የአፍላ ወጣቶች እና የወጣቶች ዓመታዊ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ወጣቶች የነገ ሀገር ተረካቢ በመሆናቸው ጤናማ እና ብቁ ዜጎች ሊሆኑ ይገባል ብለዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴርም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ለአፍላ ወጣቶች እና ወጣቶች ጤና መበልጸግ በትኩረት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ በበከላቸው÷ ሚኒስቴሩ የዜጎችን ጤና ለማበልጸግ የተለያዩ ግቦችን አስቀምጦ እየሠራ መሆኑን ጠቁመው÷ ከእነዚህ መካከል የወጣቶች ጤና ከፍተኛ ትኩረት እንደተሰጠው ገልጸዋል፡፡ አፍላ ወጣቶች በጤናቸው ላይ ጉዳት ከሚያደርሱባቸው አጋጣሚዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁ እና ቤተሰቦቻቸውን ጭምር በማንቃት ትልቅ አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

እንደ “ስኩል ሄልዝ” አይነት ፕሮግራሞች ተቀርጸው ተግባራዊ መደረጋቸውን እንዲሁም የተለያዩ የወጣቶች ጤና ስትራቴጂዎች ተነድፈው እየተተገበሩ ነው ማለታውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ባለድርሻ አካላትም ለወጣቶች እና አፍላ ወጣቶች ጤና በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ተናግረው የበኩላቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!