Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የመውሊድ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 1 ሺህ 497 ዓመት የነብዩ መሐመድ መውሊድን በዓል አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

የዘንድሮው መውሊድ ነብዩ ሙሀመድ ለመላው ዓለም የተላኩ በመሆናቸው የእሳቸውን ልህቀት በሚገልፅ መልኩ”የእዝነቱ ነቢይ” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር አስታውቋል።

ነብዩ ሙሀመድ ሀበሻን ከእቅፍ እስከ ህልፈታቸው ድረስ በልዩ ሁኔታ ያውቋት ነበር ያለው መግለጫው÷ በዚህ ምክንያት መውሊድ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ዘንድ የሚከበረው በልዩ ክብርና ኩራት መሆኑን ጠቁሟል፡፡

በመግለጫው እንደተጠቀሰው÷ የነብዩ መሐመድ ፈለግን በመከተል ስብዕናቸውን በመላበስ ወደ ሰላም የሚወስዱ መልካም ተግባራትን ማከናወን ይግባል ብሏል ።

መውሊድ ሁሉም የተቸገሩ ዜጎች የሚረዱበት እንዲሆን የጠየቀው ምክር ቤቱ÷ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱን አስተላልፏል።

በምንተስኖት ሙሉጌታ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.