ዓለምአቀፋዊ ዜና

ቤላሩስ የኒውክሌር የጦር መሳሪያ ጥቃት እንደሚያሰጋት አስታወቀች

By Melaku Gedif

October 07, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በፖላንድ ያላት የአቶሚክ መሳሪያ ለኒውክሌር መሳሪያ ሊያጋልጠኝ ይችላል ስትል ቤላሩስ ገለጸች።

ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሉካሸንኮ ፖላንድ በቤላሩስ ላይ የኒውክሌር ጥቃት ልታደርስ የምትችልበት እድል ሰፊ ነው በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ቤላሩስ የኒውክሌር የጦር መሳሪያ ስሌሌላት አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፥ በጉዳዩ ላይ ከክሬምሊን እንወያያለን ብለዋል።

ፖላንድ እና ዋሺንግተን የኒውክሌር መሳሪያን መጋራት በሚችሉበት ዙሪያ በመምከር፥ ፖላንድ አሜሪካ የኒውክሌር መሳሪያዎቿን ማስቀመጥ እንድትችል ይሁንታ መስጠቷን ተከትሎ ነው ፕሬዚዳንቱ ስጋታቸውን የገለጹት።

አሜሪካ በበኩሏ ኔቶን ከፈረንጆቹ 1997 በኋላ በተቀላቀሉ አባል ሀገራት ግዛት የኒውክሌር ጦር መሳሪያ የመትከል ዕቅድ እንደሌላት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቬዳንት ፓተል መግለጻቸውን አር ቲ ዘግቧል።

አሜሪካ የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎቿን በቤልጂየም፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ኔዘርላንድስ እና ቱርክ ውስጥ የተከለች ሲሆን፥ ሩሲያ እነዚህ የጦር መሳሪያዎች ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ ብትጠይቅም አሜሪካ እና ኔቶ ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡