Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ላይ በተጣለው ያልተሳካ ማዕቀብ አውሮፓ “ቀስ በቀስ እየደማች ነው” – የሃንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ኅብረት ሩሲያ ላይ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ የሃንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን ጠየቁ፡፡

ቪክቶር ኦርባን ÷ “ማዕቀቡ የሩሲያ እና የዩክሬንን ጦርነት ያላስቆመ በመሆኑ አውሮፓን ከመጉዳት ውጪ ምንም የፈየደው ነገር የለም” ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ÷ አውሮፓ እንዲያውም ቀስ በቀስ እየደማች መሆኑን ጠቅሰው ሩሲያ ግን በመሀል ከሁኔታው እየተጠቀመች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

“የብራሰልስ የከሸፈው ፖሊሲ መለወጥ አለበት” በሚል የሚቀነቀነውን ሐሳብ ግልጽ እንደሆነ እና እርሳቸውም እንደሚደግፉት ተናግረዋል።

የሃንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን መግለጫ ያወጡት የአውሮፓ ኅብረት በሩሲያ ላይ ሥምንተኛ ዙር ማዕቀብ መጣሉን ባወጀበት ቀን መሆኑን አር ቲ ዘግቧል።

አዲሶቹ የኅብረቱ ማዕቀቦች የነዳጅ ዋጋ ላይ ገደብ መጣል ፣ እስከ 7 ቢሊየን ዩሮ የሚደርስ የንግድ ማዕቀብ እንዲሁም በ30 ሰዎች እና በሰባት አካላት ላይ የተጣሉ የመዘዋወር ገደቦችን አካቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.