ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንጂባራ ዩኒቨርሲቲ ግቢውን ለመማር ማስተማር ምቹ ለማድረግ ያከናወነውን ስራ አደነቁ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንጂባራ ዩኒቨርሲቲ ግቢውን ለመማር ማስተማር ምቹ ለማድረግ ያከናወነውን ስራ አደነቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ የእንጂባራ ዩኒቨርሲቲ ግቢውን ለመማር ማስተማር ምቹ ለማድረግ አስተማሪ የሆነ ሥራ ሠርቷል ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲው ግቢውን በማሳመር የሠራውን አኩሪ ሥራ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ችግር በመፍታትና በዓለም ደረጃ የሚወዳደሩ ልሂቃንን በማፍራት ይደግማል ብዬ አምናለሁም ነው ያሉት።