ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ሀዲያ ሆሳዕና እና አዳማ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል

By Feven Bishaw

October 07, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁለተኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀዲያ ሆሳዕና እና አዳማ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል፡፡

ዛሬ ምሳ ሰዓትና ከከሰዓት በኋላ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡

በዚህም 7 ሰዓት ሀዲያ ሆሳዕና ከሲዳማ ቡና ጨዋታቸውን ያደረጉ ሲሆን÷ ሀዲያ ሆሳዕና 4 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የሀዲያ ሆሳዕናን የአሸናፊነት ጎሎች ፍቅረየሱስ ተወልደብርሀን፣ብሩክ ማርቆስ፣ ፀጋዬ ብርሀኑ እና ባዬ ገዛኸኝ ሲያስቆጥሩ ሲዳማ ቡናን ከሽንፈት ያልታደገችውን ግብ ያኩቡ መሐመድ አስቆጥሯል፡፡

10 ሰዓት መቻል ከአዳማ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ በአዳማ ከተማ 2 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

የአዳማ ከተማን ግቦች ዳዋ ሆቴሳና አሜ መሃመድ አስቆጥረዋል፡፡