Fana: At a Speed of Life!

በ239 ሚሊየን ዶላር የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና የሳኒቴሽን ልማት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በ239 ሚሊየን ዶላር በ5 ዓመታት ተግባራዊ የሚሆን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ የሳኒቴሽን ልማት እና የኃይል አቅርቦት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።

የፕሮጀክቱ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የትምህርት ሚኒስቴር፣ የገንዘብ ሚኒስቴር እና የወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በምስራቅ ሸዋ ዞን ጊምቢቹ ወረዳ ጨፌ ዶንሳ ከተማ ተከናውኗል።

የፕሮጀክቱ ክንውን “ወተር ፎር ላይፍ ፕላስ ፕሮጀክት” በሚል በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ የሳኒቴሽን እና የኃይል አቅርቦት ልማት ፕሮግራም የሚከናወንበት ይሆናል።

የፕሮጀክቱ ስራ በችልድረን ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን 128 ሚሊየን ዶላር እና በኢትዮጵያ መንግስት 111 ሚሊየን ዶላር ወጪ ይተገበራል።

ፕሮጀክቱ በስምንት የተለያዩ ክልሎች የመሰረተ ልማት ባልተዳረሰባቸው ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋማት እና ለአካባቢው ማህበረሰብ በአምስት ዓመታት ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የውሃና እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ፥ ፕሮጀክቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን የንጽህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት እቅድ ለማሳካት ያግዛል ብለዋል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ በበኩላቸው የፕሮጀክቱ መተግበር በጤና ተቋማት የሚስተዋለውን የውሃና የሳኒቴሽን ችግሮች ያቃልላል ማለታቸውን የኢዜአ ዘገባ መላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.