Fana: At a Speed of Life!

የ12 ኛ ክፍል ተፈታኟ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ወንድ ልጅ ተገላገለች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመፈተን ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደበች ተማሪ ወንድ ልጅ በሠላም መገላገሏ ተገለፀ።

ከቡርቃ ዲምቱ መሰናዶ ትምህርት ቤት ድሬደዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደበችው ተማሪ ጽጌረዳ አበራ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመፈተን ዩኒቨርሲቲ ከደረሰች በኋላ ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግላለች።

ተማሪ ጽጌረዳ አበራ በዛሬው ዕለት ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ወንድ ልጅ በሰላም መገላገሏን ነው የዩኒቨርሲቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን እና የሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ኮማንድ ፖስት ዘርፍ የህክምና ግብረ ሀይል አስተባባሪ ዶክተር ሁሴን መሀመድ የገለጹት፡፡

በአሁኑ ሰዓት እናትና የተወለደው ህፃን በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡

በተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.