የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By Mikias Ayele

October 08, 2022

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስሰር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺሕ 497ተኛው የነብዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) የልደት በዓል (መውሊድ) አደረሳችሁ ብለዋል።

በመውሊድ የተቸገሩትን በመርዳት፣ ለታመሙት ዱዓ በማድረግ፣ በአዛኝነት እና በመተሳሰብ  እንዲከበርም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለዕምነቱ ተከታዮች በዓሉ የሰላም እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡